Articoli correlati a ሞት በውክልና

ሞት በውክልና - Brossura

Obsse, Hailu Worku

 
9798223362517: ሞት በውክልና

Sinossi

አንድ ሰው ነበረ፤ የተለየ ልብ ያለው። አኧምሮውን ማዘዝ እና ማስቆም የሚችል ልብ። አኧምሮው ሲያስቆመው አካሉም እዛው ተገተረ። ያለ ተስፋ፣ ያለረዳት፣ እዛው እንድቆመ ፤ ለምን እንደሆነ ባላወቀው ምክንያት፣ ሁሉም ነገር በዙሪያው በፍጥነት ይለዋወጥ ነበር። ለተመለከተው ፊቱ ይናገራል፣ እሱ ለውጡ አልገባውም። እዛው በመንገዱ ዳር እንደቆመ መልኩ ጠፉ፣ ውበቱ ረገፈ። ዓመታት አለፉ። 

መንገደኛው ሁሉ ይህ ሰው ብቸኛ ነው ብሎ ያዝናል። እሱ ግን ለምን እንደታዘነለት፣ ነገሮችም ሁሉ እየተለወጡ መሆናቸውን አያውቅም። በዚያች ቦታ ለዓመታት ከመቆሙ የተንሳ፣ እርሱ የቦታው ምልክት ሆኗል። ሰው ሁሉ ቦታውን ለመለየት የተለየ ሥዕሎች እና ማስታወቂያ አላስፈልገውም።

ሰዎች እሱን እዚያ ቦታ ላይ ለሲሶ ምዕተ ዓመት ያህል ዘመን የገተረው ጉዳይ ምን እንደሆነ አያውቁትም፣ ቢያውቁትም አይገባቸውም። ምክንያቱም ሰዎች ሁሉ እሱ ያለው ዓይነት ልብ የላቸውም ! ይህ መፅሐፍ ግን ስለእርሱ ሳይሆን፤ እርሱ ስለሚያውቃት፣ እና መኖርም መሞትም አቅቷት ስለምትሰቃይ ሴት እንጂ።

Le informazioni nella sezione "Riassunto" possono far riferimento a edizioni diverse di questo titolo.